"ስለ ቶንሲል የምናውቀው አና የምንሳሳተው ምንድን ነው?"

ቶንሲል ምንድን ነው?

ቶንሲል ለብዙዎቻችን እንደሚመስለን በሽታ አይደለም።

ቶንሲል ማለት ትንንሽ አበጥ ያሉ የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ አካላት ስብስብ ነው። ይህም በክብ ቀለበት ከምላስ ጀርባ የላንቃን የጎን ግድግዳ እና የላንቃን ክዳንና የአፍንጫን የውስጠኛ ክፍሎች ያስተሳስራል።

- ቶንሲል ጥቅሙ ምንድን ነው? በአፍም በአፍንጫም የሚገቡ ተዋህስያንን መዋጋት ነው። የሰውነትን በር ከጠላት መከላከያ ነው።

- ቶንሲል እና እንጥል አንድ ናቸው?
ሁለቱም በላንቃ አካባቢ ይገኛሉ። ግንኙነታቸው ግን ጉርብትና እንጅ በአገልግሎት አይገናኙም።

- Uvula/እንጥል
እንጥል ማለት ከላንቃ ላይ የተንጠለጠለ ማለት ነው። ከቶንሲል ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።

- የቶንሲል ህመም/tonsialiophayngitis?
ይህ የቶንሲል እና የላንቃ አካባቢ በተዋህስያን መወረር ነው።

- የህመም ምልክቶች
ትኩሳት ፣ ለመዋጥ መቸገር ፡ ራስ ምታት ፣ የአፍ መሽተት ፣  የአንገት ንፍፊት እብጠት ፣ ማንኮራፋት ፣ ሳል

የቶንሲል ህመም መተላለፊያ መንገዶች
1. በትንፋሽ ጠብታ
2. በንክኪ

- የባክቴሪያ ቶንሲል በብዛት የሚያጠቃው ማንን ነው?

የባክቴሪያ ቶንሲል ከሁለት አመት በላይ የሆኑ ህጻናትን የሚያጠቃ ሲሆን አብዛኛዎቹ ከ5-15 እድሜ ያሉት ይጠቃሉ። የቫይረስ ሲሆን ለጋ ህጻናትም ይጠቃሉ።

የቶንሲል ህመም ተያያዥ ችግሮች
1 ፡ መግል መቋጠር  tonsiar, peritosilar or retropharyngeal abscess
2. የሳንባ ምች / የማጅራት ገትር
3. የልብ ህመም rheumatic heart disease ይህን ለመከላከል ቶንሲል እንዳመመን ወደ ጤና ተቋም መሄድ።
4. የኩላሊት ህመም PS glomerulonephritis
5. የቶንሲል መፋፋት adenotonsilar hyperthrophy

- የቶንሲል ህመም ህክምና
መጀመሪያ የባክቴሪያ ወይስ የቫይረስ ነው  የሚለውን መለየት ያስፈልጋል።

መለያ መንገዶች
1. የቫይረስ ከሆነ የጉንፋን ምልክት አብሮ ይኖራል ግን አንዳንድ ጊዜ እንደ ቫይረስ ጀምሮ ወደ ባክቴሪያ ሊቀየር ስለሚችል ጥንቃቄ ይፈልጋል።
2. መግል የያዘ ከሆነ የባክቴሪያ ምልክት ነው ግን ይህን በደንብ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል።
3. ድድ፣ ከንፈር ወይም ምላስ የቆሰሉ ከሆነ የቫይረስ ምልክት ነው።
4. የነጭ የደም ሴል እና ተያያዥ ምርመራ

መድሃኒት
1. የህመም ማስታገሻ
2. እንደ ቶንሲሉ ህመም መነሻ የተለያዩ ጸረ ባክቴሪያ አለበለዚያም ፀረ ቫይረስ መድሃኒት
3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ ረፍት ማድረግ።
4. ማር እና የውሃ ኢንፋሎት መታጠን
5. የብርቱካን ወይም ሎሚ ጭማቂ።