የጡት ካንሰር በወንዶች ላይ ይከሰታልን?

የወንዶች የጡት መጠን አንዲት ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ሴት የሚኖራትን ያህል ጡት ነው፡፡
በዚህም የተነሳም መጠኑ ከሴቶች በጣም ያነሰ ይሁን እንጂ ወንዶች በጡት ካንሰር የመያዝ እድል አላቸው፡፡ የወንዶችን የጡት ካንሰር ከሴቶች አቻወቻቸው በምን ይለያል?
 
1.የወንዶች የጡት ካንሰር ከጠቅላላው የጡት ካንሰር 5% ወይም አንድ ወንድ የጡት ካንሰር ሲከሰት በሴቶች ደግሞ ከ150-200 ሴቶች ላይ ድረስ ይከሰታል (1∶150-200) ፡፡
 
2.በወንዶች ላይ የሚከሰተው የጡት ካንሰር በአብዛሃኛው ጊዜ የሚታወቀው (Diagnose) የሚደረገው ዘግይቶ ነው፡፡
 
ለዚህም እንደዋነኛ ምክንያት የሚቀመጠው ወንዶች በጡት ካንሰር እንያዛለን ብለው ስለማያስቡና ተገቢውን ምርመራ በጊዜ ስለማያደርጉ ነው፡፡
ከዚህ በተረፈ ግን ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው የሴትና የወንድ የጡት ካንሰር ተማሳሳይ ህክምናና የመዳን እድል አለው፡፡
 
የወንዶች የጡት ካንሰር አጋላጭ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
የእድሜ መጨመር (ብዙው የጡት ካንሰር የሚከሰተው ከ 60 አመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው) የጡት ካንሰር በቤተሰብ (አባት፤ እናት፤ እህት፤ወንድም) ውስጥ መኖር
ጡት ወይም ደረት አካባቢ በልጅነት የጨረር ህክምና ማድረግ በተለያዩ መድሀኒቶች ወይም ኢንፌከሽን ምክንያት የጡት መጠን መጨመር (Gynecomastia) ኢስትሮጅን የሚባል መድሀኒትን መውሰድ ከልክ ያለፈ ውፍረት